ከ90 በመቶ በላይ በጋዛ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መዉደማቸዉ ተገለጸ

Date:

በጋዛ የተደረጉ ጥናቶች እንዳመላከቱት ከ90 በመቶ በላይ በጋዛ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ወድመዋል ተብሏል፡፡

የጋዛን ነዋሪዎች ማንነትን የሚገልጹ እንደ ባህልና የእምንት ታዎችን እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን በማጥፋት አለምአቀፉ ገለልተኛ የምርመራ ኮሚሽን  እስራኤልን  ተጠያቂ አድርጓል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የአለምአቀፍ ገለልተኛ የምርመራ ኮሚሽን ይዞት በወጣዉ ሪፖርት እስራኤል የፍልስጤማዊያንን ማንነት ከምድር ለማጥፋት እንደ ትምህርት ቤቶችና የሃይማኖት ተቋማት ላይ የጥፋት ወንጀል እያደረገች ነዉ ብሏል፡፡

ከዚህ በፊት ኮሚሽኑ ባወጣዉ ሪፖርት እስራኤል በጋዛ ግጭት ወቅት የሴቶችን የጤና መጠበቂያ ተቋማትን ስልታዊ በሆነ መንገድ በማጥፋት ፍልስጤማውያን ላይ “የዘር ማጥፋት ድርጊቶችን” ፈጽማለች በማለቱ፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሪፖርቶቹ አድሎአዊ እና ፀረ ሴማዊ ናቸው በማለት ወቅሰዋል፡፡

በዚህ ምክኒያት እስራኤል ከኮሚሺኑን እራሷን ማግለለዋን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታዉቋል፡፡

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የነበሩት የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒሌይ “እስራኤል በጋዛ ውስጥ እያደረሰችዉ ያለዉ ጉዳት እየጨመረ መምጣቱን እያየን ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በትምህርት ተቋማት፤በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ቦታዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን የመረመረ ሲሆን በምርመራዉም አለም አቀፍ ህጎች መጣሳቸዉን አረጋግጫለሁ  ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...