ዩክሬን ባለፈው ሳምንት 1400 የሚሆኑ አፍሪካውያን በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት እየተዋጉ መሆኑን ገልፃ እንደነበር ሲታወስ ኬንያ ከ200 የሚበልጡ ዜጎቿ ለሩሲያ እየተዋጉ ስለመሆኑና በርካታ ኤጀንሲዎች አሁንም ምልመላ እያደረጉ መሆኑን አስታውቃለች።
የኬንያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የምልመላ መረቦቹ በኬንያና በሩሲያ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሶ በሞስኮ የሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ በጦርነቱ የተጎዱ ሰዎችን መመዝገቡንና ሰዎቹ እስከ 18,000 ዶላር ድረስ ሊከፈላቸው ቃል እንደተገበላቸው ገልጿል።
ባለፈው መስከረም ኬንያ በናይሮቢ አቅራቢያ ለጦርነቱ ምልመላ ሲያደርግ የነበረን ግለሰብ መያዟና ሊላኩ የነበሩ 21 ዜጎቿን ማትረፏ ይታወሳል።
በተጨማሪ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶም በዩክሬን የተያዙ ኬንያውያን እንዲለቀቁ የዩክሬን አቻቸውን መጠየቃቸው ይታወሳል።
ዘገባው የአልአረቢያ ነው።
@TikvahethMagazine
