“ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ስማርት ስልክ አይጠቀሙ”

Date:


          
   3 የአውሮፓ ሃገራት እና ካናዳ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ  ዚጎቻቸው ስማርት ስልኮችን እንዳይጠቀሙ ፥ ይልቁንም በርነር ስልኮችን በመያዝ ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳሰቡ፥ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሰዎች ላይ ስልክና ላፕቶፕን ጨምሮ በኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ላይ የሚደረገው ምርመራ ተጓዦች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እያደረገ እና መጉላላትን እየፈጠረ በመሆኑ ይህንን ለመከላከል ስማርት ያልሆነውን በርነር ስልክ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ከዚህም በተጨማሪ በርነር ሥልክ የማይጠቀሙ እና ስማርት ስልኮችን ይዘው የሚጓዙ ከዲጅታል አካውንታቸው ማለትም ኢሜልና ማህበራዊ ገፆቻቸውን ሳይን አውት እንዲያደርጉ ማሰሰቢያ ተሰጥቷል።

በርነር ስልኮች የድምጽ እና ጽሁፍ መልዕክት ብቻ የሚያስተላልፉ ፣ኢንተርኔት መጠቀም የማይችሉ ራስን ከክትትል የሚጠብቁ በየሱቁ የሚገኙ ርካሽ ስልኮች ሲሆኑ ፣በርነር የሚል ስያሜ ያገኙትም ግዚያዊ እና ተግባራቸውን እንደፈጸሙ የሚጣሉ ወይንም የሚቃጠሉ በመሆናቸው እንደሆንም መረዳት ተችሏል።

ከካናዳ በተጨማሪ ይህንን ማሳሰቢያ ወደ አሜሪካ ለሚጓዙ ዜጎቻቸው  ያወጡት ሃገራት ፈረንሳይ ፥ ጀርመን እና ዴንማርክ ሲሆኑ፥በትራምፕ አስተዳደር ላይ ትችት የሰነዘሩ እና ለስብሰባ ወደ አሜሪካ የተጓዙ ፈረንሳዊ  ሳይንቲስት ስልካቸው ላይ ትችታቸው በመገኘቱ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ትራቭል እንድ ቱር ዎርልድ ዛሬ እንደ አውሮፓውያነ (-April 18/2025)

ሉዓላዊ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...