ዋና ጸሐፊ ከኡጋንዳ የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ኅብረት ስራ ሚኒስትር ምዌብሳ ፍራንሲስ ጋር ተወያዩ

Date:


ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ሲሆኑ የሁለቱ አካላት ውይይትም በተለይም በኢኮኖሚ እና ቢዝነስ መስች ያሉ እድሎችን ለጋራ ተጠቃሚነት ማዋል እንዲቻል ያግዛል ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ለውጦች እና ምቹ የቢዝነስ ከባቢ ለመፍጠር ምክር ቤቱ በሚያከናውናቸው የንግድና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን፣ የአቅም ግንባታ፣ የምርምርና አድቮኬሲና ሌሎች ስራዎች ዙሪያ ገልጸውላቸዋል፡፡


ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ እንደ ኡጋንዳ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ጋር በመተባበር በአህጉሩ ያለውን የገበያ እድል መጠቀም እንደሚገባ አብራርተውላቸዋል፡፡


ሚኒስትሩ ምዌብሳ ፍራንሲስ በበኩላቸው የኡጋንዳን የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ለማጠናከር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተሞክሮ የተሻለ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ከምክር ቤቱ ጋር ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡


የሁለቱ ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶችም ተቀራርቦ በመስራት የሀገራቱ ቢዝነሶች በጋራ ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን አማራጮች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም በውይይቱ ተነስቷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...