የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የደን ቀን ”ደንና ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም ደንን መጠበቅ የሀገርን የረዥም ግዜ የኢኮኖሚ ዋስትናን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።
የደን ሀብት ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 8 ነጥብ 1 በመቶ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።
ዘላቂ የደን ሀብት ልማት በዘመናችን የተጋረጠውን የአየር ንብረት ለውጥ፣ የበርሃማነት መስፋፋት፣ የብዝሃ ሕይወት መመናመን፣ የስነ ምህዳር መዛባትን፣ የምርትና ምርታማነት መቀነስን ለመከላከል ወሳኝ ነው ብለዋል።
