ዘለንስኪ የቀድሞ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ዩክሬንን እንዲመሩ ሃሳብ አቀረቡ

Date:

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ፣ የዩክሬን የመጀመሪያዋ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሊያ ስቪሪደንኮ፣ የሀገሪቱን መንግሥት እንዲመሩ ሀሳብ ማቅረባቸው ተገለፀ።

ዩክሬን የአቀደችው ግብ ወደ ስኬት እንዲደርስ የአስፈፃሚ አካል ለውጥ ልታደርግ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ  አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ከመጀመሪያዋ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር  የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት፣ የሀገር ውስጥ የጦር መሣሪያዎችን ምርት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ መወያየታቸውን ገልፀዋል።

ዩሊያ ስቪሪደንኮ እኤአ በህዳር 2021 የመጀመሪያዋ የዩክሬን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑ ሲሆን፤ ከዚህ ሀላፊነታቸው በፊት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...