የሀገር ዉስጥ ብድር ክምችት 2.3 ትሪሊዮን ብር መድረሱ ተነገረ

Date:

የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ብድር መጠን በተመለከተ የወጡ የተሳሳቱ ዘገባዎችን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ እንደገለጸው፣ እ.ኤ.አ እስከ 2024 መጨረሻ ድረስ የኢትዮጵያ የውጭ ብድር መጠን የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ጨምሮ 31.6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ብድር ክምችት ደግሞ 2.3 ትሪሊዮን ብር ደርሷል ብሏል።

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር የወጣውን ሪፖርት በማጣቀስ፣ “እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር መድረሱ ተነገረ” በሚል ርዕስ የወጣው ዘገባ ላይ ግድፈቶች እንዳሉ የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል። ዘገባው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ እስከ 2023 ድረስ የነበራትን የውጭ ዕዳ መጠን 28.5 ቢሊዮን ዶላር ሆኖ ሳለ 62.5 ቢሊዮን ዶላር በማለት ማቅረቡ የተሳሳተ መሆኑን ሚኒስቴሩ አብራርቷል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ብድር በአብዛኛው የተጠራቀመ ውርስ ዕዳ (legacy debt) መሆኑን ጠቁሞ፣ መንግሥት ባለፉት ሰባት ዓመታት ይህንን የክፍያ ጫና ለመቀነስ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...