የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከቼክብሔራዊ ሙዚየም እና ከቼክ ዲቨሎፕመንት ኤጀንሲ ሀላፊዎች ጋር ስምምነቱን በፕራግ ከተማ በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ህፃናትን ማእከል ያደረገ ዘመናዊ ሙዚየምመገንባት የሚያስችል ሲሆን የቼክ ሪፐብሊክ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።
ይህ ቋሚ የልጆች ሙዚየም በወዳጅነት ቁ.2 ፓርክ ውስጥ የሚገነባ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ የህፃናት ሙዚየሙ ህፃናት ቀለል ባለ መንገድ ስለ ሀገራችን ታሪክ እና ባህል እውቀት እንዲኖራቸው ከማስቻልም በላይ በፈጠራ፣ በትምህርትና በእውቀት እንዲጎለብቱ እድል የሚፈጥርላቸውመሆኑን ገልፀዋል።
የቼክ መንግስት ይህንን ሙዚየም ለማቋቋም ለሚያደርገው የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
(አራዳ ኤፍ ኤም)
