ሁለቱ የከርሰ ምድር ውሃዎች ደርቀዋል

Date:

“ ሁለቱ የከርሰ ምድር ውሃዎች ደርቀዋል፤ ችግሩ አሁን የባሰ ደረጃ ደርሷል። የውሃ ችግሩን ለመቅረፍ 18 ሚሊዮን ብር ይጠይቃል ” – ድርጅቱ

በሥሩ እስከ 5000 ሰዎችን የሚያንቀሳቅሰው ሰላም የህፃናት መንደር በሚገኝበት አዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የውሃ ችግር እንደተጋረጠበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

ድርጅቱ ይህን ያለው የውሃ ጉድጓድ ለመቆፈር የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ አዘጋጅቶት በነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ፕሮግራም ነው።

አቶ ጎይቶም ተ/ሚካኤል በሰላም የህጻናት መንደር የሮፋም ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ምን አሉ ?

“ ከሦስቱ የከርሰ ምድር ውሃዎች ሁለቱ ደርቀዋል፡፡ አንዱ በጣም በትንሹ ውሃ እየሰጠን ይገኛል፡፡ ከእድሜ ብዛትና የከተማ አካባቢ በመሆኑ በአካባቢያችን በርካታ የውሃ ጉድጓዶች እየተቆፈሩ በመምጣታቸው አጭር ጥልቀት ስላለው እጥረት ገጥሞናል።
 
በመሆኑም ወዳጆች፣ አብረውን የሚሰሩ ፓርትነሮችን ጠርተን የውሃ ጉድጓድ በራስ አቅም ተረዳድተን መቆፈር እንድንችል የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ፕሮግራም ለማዘጋጀት ወስነናል ” ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ ምን ያክል ገንዘብ ያስፈልጋል ? የውሃ ችግሩ እንዴት አደረጋችሁ ? በችግሩ ሳቢያ ለምን ያክል አላስፈላጊ የውሃ ወጪ እየተዳረጋችሁ ነው? ስንልም አቶ ጎይቶምን ጠይቀናል።

ምን መለሱ ?

“ በትንሹ እስከ 8 ሊትር ውሃ በሰከንድ ውስጥ ሊሰጥ የሚችል 350 ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ መቆፈር ያስፈልጋል፡፡

ዋጋው በአሁኑ ሁኔታ እስከ 18 ሚሊዮን ብር  ይጠይቃል። የውሃ ችግሩ ከባድ ችግር ነው፡፡ ያለችን የከርሰ ምድር በሰከድ አንድ ሊትር ውሃ ነው የምትሰጠን፡፡ የመንግስት ውሃ በመካከል አክሰስ አለን፡፡ ግን በፕሮግራም ስለሆነ ብዙ ማግኘት አልተቻለም፡፡

ችግሩ አሁን የባሰ ደረጃ ደርሷል፡፡ ያለችው የጉድጓድ ውሃ ከተቋረጠች ችግሩ በጣም የከፋ ይሆናል፡፡ በቀን አምስት ቦቴ ውሃ እናስመጣለን፤ ያ ማለት በትንሹ 4000 ብር ነው አንድ ቦቲ፡፡ የከርሰ ምድር አማራጭ ውሃ ባለመኖሩ በወር 200 ሺሕ ብር እያስወጣን ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

ሰላም የህፃናት መንደር ማነው ?

ድርጅቱ ከተመሰረተ ከ38 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ፣ በመጀመሪያው ወላጆቻቸውን በተለያዬ ምክንያቶች ያጡ ለማሳደግ የተነሳ፣ በኋላም ሌሎች አገልግሎቶችንም እየሰጠ የኖረና የሚገኝ ነው፡፡

ወደ 300 ወላጅ አልባ ህጻናትን ያሳድጋል፡፡ በትምህርት ቤቱ 3000 ተማሪዎችን ያስተምራል፡፡ ወደ 200 የሚሆኑ ህፃናትን በማቆያዎች አሉት። በማሰልጠኛ ተቋሙ 1000 ሰልጣኞችን ይገኛሉ፡፡ በክልኒኩ በትንሹ በቀን ከ1000 በላይ ሰዎች ይታከማሉ።

#NB : በትላንትናው የገቢ ማሰባሰቢያ ምሽት 10 ሚሊዮን 200 ሺሕ ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ አሁንም በቴሌ ብር በቁጥር #0993242424 ድጋፍ ማድረግ የሚቻል መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

#TikvahEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...