«የሙዚቃ አድማጩ ከኔ የተለየ ነገር መጠበቁን አከብራለሁ» ድምፃዊት የሺ ደመላሽ

Date:

ድምፃዊት የሺ ደመላሽ “ውብሰው” ስትል የሰየመችውን ሁለተኛ የስቱዲዮ አልበሟን ከሰሞኑ ለአድማጭ አቅርባለች::

ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረገችው ድምፃዊቷ አስር ሙዚቃዎች የተካተተበት ስራዋ በሰፊው የደከመችበት እንደነበር ተናግራለች::

«ለእኔ አልበም እንደ መፅሀፍ ነው። እያንዳንዱ ዘፈን ምዕራፍ ሆኖ በውስጡ የተለያየ ሃሳብ እንዲይዝ ይደረጋል ይህም ጊዜ ይወስዳል»ብላለች::

በአልበሟ በሙዚቃ ቅንብርም ሆነ በግጥም እና ዜማ ረገድ “ቅኔ” ከሚለው አልበሟ ተሽላ መምጣቷን ገልፃ ከራሷ ባለፈ ስመጥር ባለሙያዎችም እንዲሳተፉበት መደረጉን ትጠቅሳለች።

«የበዛው ግጥም እና ዜማ በእኔ ቢሰራም ወንደሰን ይሁብ አንተነህ ወራሽ በቅንብሩ ደግሞ ሚካኤል ኃይሉን ጨምሮ ባለተሰጥኦ ወጣቶች እድል እንዲያገኙ አድርጌያለሁ»ስትል ተናግራለች::

የሺ ደመላሽ በተስጥኦ ውድድር ዳኝነት በመቀጠል በድምፃዊነት በሙዚቃ አፍቃሪው ዘንድ የምትታወቅ ሲሆን በተሰጥኦ ውድድር ላይ የምትሰጭው ጠንካራ አስተያየት ሰው ካንቺ ብዙ እንዲጠብቅ አያደርገውም ወይ? ስንል ጠይቀናት

«የሙዚቃ አድማጩ ከኔ የተለየ ነገር መጠበቁን አከብራለሁ ነገር ግን የሙዚቃ ትምህርት ቤት የገባሁት ዳኛ ሳይሆን ጥሩ ድምፃዊት እሆናለሁ ብዬ ነው። ውድድሮች ላይ እኔ የምገልፀው ሳይንሱን ነው ይህም በእውቀት የመጣ ነው። የተግባሩ ደግሞ ሌላ ልምድ ነው። በዚህ ረገድ ብዙ ርቀት ሄጃለሁ ባልልም ሙዚቃ ነብሲያዬ እና ልተወው የማልችልው እንደሆነ ቢታወቅ መልካም ነው» የሚል ምላሿን ሰጥታለች።

ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...