የጋዛ የእርዳታ ጣቢያዎች ተዘጉ

Date:

የእስራዔል ጦር በጋዛ የእርዳታማሰራጫ ጣቢያዎችን መዘጋቱን አስታወቀ።

ጦሩ ባወጣው መግለጫ ወደ እርዳታ ጣቢያዎች የሚያመሩ መንገዶች እንደ “ጦርነት ቀጠና” ይቆጠራሉ ሲል አስጠንቅቋል።

የጋዛ ሰብአዊ ፋውንዴሽን ጣቢያዎቹ “ለማዘመን እና አደረጃጀትና አፈጻጸማቸውንለማሻሻል” መዘጋታቸውን አስታውቋል።

በትናንትናው ዕለት የእስራዔል ጦር በእርዳታ ማደያ ጣቢያ አቅራቢያ በከፈተው ተኩስ 27 ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።

በወቅቱ የእስራዔል ጦር በእርዳታ ማደያ ጣቢያው አቅራቢያ ተጠርጣሪ ግለሰቦችወደ እነርሱ እያመሩ በነበረበት ወቅት ተኩስ መክፈታቸውን ነው የገለጸው።

የተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በበኩሉ የእርዳታ ማሰራጫ ጣቢያዎች
መዘጋትን ኮንኗል።

ዩኒሴፍ አሁን እየቀረበ ያለው እርዳታ እጅግ አነስተኛ ሆኖ እያለ ይህን ውሳኔመወሰን አላስፈላጊና አረመኔያዊነት ነው ብሏል።

በጋዛ የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ጀምስ ኤልደር በርካታ ታዳጊ ህጻናት ከ15 እስከ
20 ኪሎ ሜትር እርዳታ ፍለጋ በእግራቸው ይጓዛሉ ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...