በኢስታንቡል የተደረሠው የጦር እስረኞች ልውውጥ ስምምነት “ጠንካራ እርምጃ” እና “ተስፋ ሰጪ ምልክት ነው” ሲሉ ኢትዮጵያዊው የፖለቲካ ሳይንስ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ በፍቃዱ ዳባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
👉 ምሁሩ በቀጥታ የሰላም ድርድሩ አውድ የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ በሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት ገለልተኛ የነበሩቱ “አሸናፊ” እንደሚሆኑ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
🌍 ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱ ለመላው ዓለም በተለይም የሩሲያ እና ዩክሬን ቀውስ በፈጠረው ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ለተጎዱ የአፍሪካ ሀገራት ጠቃሚ እንደሚሆን ባለሙያው ጠቁመዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
