የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የፈንድ እጥረት ለመቀነስ እየተሰራ ነዉ

Date:

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የገቢ ምንጭ ለማመንጨት የሶሻል ኢንተርፕራይዞች አማራጭ አድርጎ ለመጠቀም የፖሊሲ ክፍተት እንዳለ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ የሶሻል ኢንተርፕራይዞችን የሚመራ የህግ ማዕቀፍ አለመኖሩ ተገልጿል።

ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የፖሊሲ ጥናቱን እያስጠና ያለዉ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ነዉ።

ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸዉ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የፕሮጀክት አስተዳደር አጋርነት ሀላፊ አቶ እድሪስ የሱፍ ናቸዉ።

አቶ እድሪስ እንደገለጹት፤ከፈንዶች መቋረጥ ጋር ተያይዞ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ሀገር በቀል ምንጮች እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ስለመገኘቱ ገልፀዋል።

‹‹የሶሻል ኢንተርፕራይዞች በዋናነት ቢዝነስ ቢሰሩም፤ ትርፉን አትርፈዉ ያገኙትን ትርፍ ለማህበረሰቡ እርዳታ የሚያዉሉበት አሰራር በሌላዉ አለም አለ ››ሲሉም አስረድተዋል።

ሆኖም በኢትዮጵያ እንደዚህ ያሉ ተቋማትን ለማገዝ አሁን ላይ ያሉ የማያመቹ ህጎች ቅሬታ የሚያስነሱም ናቸዉ።

አቶ እድሪስ የሱፍ ‹‹እኛ ሀገር ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ሲባል ሀሳቡም አዲስ ይመስላል፤ ይሄን የሚገዛ ህግም የለም›› ብለዉናል።

ራሳቸዉን በዚህ ድርጅት ስር ያስቀመጡ ተቋማት ያላቸዉ ሚና ታዉቆ ከነጋዴ እኩል ከትርፋቸዉ የሚወሰደዉም ታክስ እንዲታይላቸዉ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ይዘጋጃል ተብሏል።

ሀላፊዉ እየተካሄደ ያለዉ ጥናት በበጎ አድራጎት እና በንግድ ትርፋቸዉ ላይ አሰራር ለማበጀት የሚያስችል ይሆናል ብለዋል።

እየተዘጋጀ ያለዉ የፖሊሲ ጥናት በስድስት ወራት ዉስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...