የሸገር ዳቦ ሽያጭ ሙሉ ለሙሉ ቆሟል

Date:

በአንበሳ አውቶብስ ሲካሄድ የቆየው የሸገር ዳቦ ሽያጭ ሙሉ ለሙሉ መቆሙን የአዲስ አአባ ከተማ ንግድ ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡

በ2012 ዓ.ም 80 ሺህ ዳቦ ያመርታል ተብሎ ወደ ስራ ለገባው የሸገር ዳቦ ምርት መሸጫ ታስበው የተዘጋጁ የአንበሳ አውቶብሶች ሙሉ ለሙሉ ስራ ማቆማቸውን የአዲስ አአባ ከተማ ንግድ ቢሮ የቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ ተናግረዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በወጣው የከተማ ስታንዳርድ ምክንያት ለሸገር ዳቦ መሸጫነት ይውሉ የነበሩ አንበሳ አውቶብሶች ከአገልግሎት እንደወጡ በመጥቀስ፣ አሁን ላይ ከተማውን በሚመጥኑ ስታንዳርድ ሱቆችና ልዩ ልዩ ማከፋፈያዎች ብቻ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ሃላፊው ለጣቢያው አብራርተዋል።

የሸገር ዳቦ ሽያጭ በሁሉም ክፍለ ከተማ በዘመናዊ ሱቆች መቅረቡ እንደሚቀጥል የገለጹት አቶ ስመኘው፤ የከተማዋን ገፅታ የማይመጥኑ የንግድ ማዕከላትን የማፅዳቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...