የኢትዮጵያ ብሔራዊ የንግድ ፖርታል የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሶስት የክልል ከተሞችን በማካተት ተመረቀ

Date:

በ2012 ዓ.ም ተጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የንግድ ፖርታል የማስፋፊያ ፕሮጀክቱን በሶስት የክልል ከተሞች ማለትም በ አዳማ፣  ባሕርዳር እና ድሬዳዋ በማድረግ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የማስፋፍያ ፕሮጀክቱን ያደረገው ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር መሆኑን ተጠቁሟል።

በምርቃት መርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ እንደገለጹት የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግስት ውጤታማ እና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

አክለውም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ጋር በተጣጣመ መልኩ፣ የኢትዮጵያን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማፋጠን ፈጠራ ያላቸውን እና ተለዋዋጭ የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ አስተዳደርን እና የዲጂታል ስራዎች የማስፋፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ የአዳማ፣ የባህር ዳር እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ያካተተ ሲሆን ይህም በዋናነት የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥን ጨምሮ የመንግስት አገልግሎቶችን በዲጂታል ሲስተም ለማቅረብ ያስችላቸዋል ተብሏል።

ማስፋፊያው በተጨማሪም ደንበኞች የሚፈልጓቸውን የአገልግሎት ክፍያዎች በኦንላይን መክፈል የሚችሉበትን አዲስ ስርዓት መዘርጋቱ ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...