የቅርስ ባለሙያዎች እገታ የቅርስ ጥገና ስራ ላይ እክል ሆኗል

Date:

ለጥገና እቅድ የተያዘላቸዉ ቅርሶችን ለመጠገን የፀጥታ ችግር ፈተና እንደሆነበት የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ገልፆል።

ይህ የተባለዉ የቱሪዝም ሚኒስትር የዘጠኝ ወር ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነዉ።

የኢትዩጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኘሮፊሰር አበባዉ አያሌዉ የቅርስ ባለሙያዎች እገታ በተለያዩ ቦታዎች መኖራቸዉን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ዘንድሮ በተለየ ሁኔታ በጣና ዙሪያ አካባቢዎች የባለሙያዎች እገታ አጋጥሟል ሲሉ አንስተዋል።

የቅርስ ጥገናዉን ለማድረግ የእገታ አደጋዉ ብዙ ቦታዎች ላይ ባለሙያ እንዳይገባ ችግር እንደፈጠረባቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልፆል።

ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞም በአማራ ክልል ማእከላዊ ጎንደር÷ ጣና ዙሪያ እንዲሁም ዋግኸምራ አካባቢዎች የጥገና ሰነዶች ተሰርተዉ ወደ ስራ መግባት አልተቻለም ተብሏል።

በበጀት አመቱ የጥገና እና እንክብካቤ ሰነድን ለመከለስ እና ለማዘጋጀት ከተያዘዉ እቅድ አንፃር አፈፃፀሙ ሰፊ ክፍተት እንደታየበት ቋሚ ኮሚቴዉ ተመልክቻለሁ ብሏል።

ቅርሶችን የማስመለስ ስራን በተመለከተ በሪፖርቱ በዘጠኝ ወራት የብራና መፅሀፍትን ማስመለስ ተችሏል ተብሏል።

ሆኖም በቀላሉ ቅርስን ለማስመለስ የማይቻል እና ብዙ የዲኘሎማሲ ስራን እየጠየቀ እንደሆነ ባለስልጣኑ ተናግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...