የብሔራዊ መታወቂያ የሌለው ባቡር መሳፈር አይችልም ተባለ

Date:


የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ አክስዮን ማህበር ከዛሬ የካቲት 24 ጀምሮ መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ እንደሚጠበቅባቸው አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ከፍተኛ የኮሙኒኬሽን ባለሞያ ወይዘሮ እስራኤል ወልደመስቀል ለኢፕድ እንደገለፁት፤ የመንገደኞችን እንግልት ለመቀነስና ለጋራ ደህንነት መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት በመቁረጥ አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ተደርጓል።

ማህበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ዲጂታላይዝድ ማድረጉን የገለፁት ወይዘሮ እስራኤል፤ ከዛሬ የካቲት 24 ጀምሮ መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም። ይህንንም ለደንበኞች የማሳወቅ ስራው ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ሲሰራ እንደነበርና ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር መታወቂያውን እንዲያገኙት እየተደረገ እንደነበር አስታውሰዋል።

የብሔራዊ መታወቂያ ተግባራዊነቱ ለሃገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ብቻ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ተጠቃሚዎች ፓስፖርታቸውን በመጠቀም ትኬት ማግኘት እንደሚችሉ ወይዘሮ እስራኤል ገልጸዋል።

በኦንላይን ትኬት የመቁረጥ አገልግሎት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል።

@ኢፕድ

💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...