የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት ለፑቲን ደብዳቤ መላካቸው የተዘገበ ሲሆን፤ በትላንቱ የአላስካ ስብሰባ ዶናልድ ትራምፕ ደብዳቤውን ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ማድረሳቸው ተነግሯል፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ የላኩት ደብዳቤ፤ በዩክሬን ግጭት ዓውድ የህጻናት ጠለፋ ክሶችን የሚጠቅስ እንደሆነ የምዕራብ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸውን ስፑትኒክ አመልክቷል።
ጉዳዩ በኢስታንቡል ድርድሮች በተደጋጋሚ መነሳቱ ተመላክቷል።
ዩክሬን ለሩሲያ የ339 ታግተዋል የተባሉ ህጻናትን ስም ዝርዝር ሰጥታለች ተብሏል።
የሩሲያው ተደራዳሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ፣ አብዛኞቹ ሩሲያ ውስጥ ገብተው እንደማያውቁ ጠቁመው፣ 50ዎቹ ጎልማሶች እንደሆኑና አንዳንድ ልጆች ቀደም ብለው መመለሳቸውን እንደገለጹ ተዘግቧል፡፡
