ቬንገር ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም በዩሮፓ ሊግ ለፍፃሜ የሚቀርቡ ከሆነ ህግ መሻሻል አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።
በፕሪሚየር ሊጉ15እና16ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክለቦች በቻምፒየንስ ሊጉ የሚሳተፏበትን እድል ለማግኘት ከጫፍ ደርሰዋል እና እንዴት ያዩታል ተብለው ተጠየቁ ።
በቢን ስፖርት በተንታኝነት ላይ የሚሰሩት አርሰን ቬንገር የእንግሊዝ ክለቦች በቻምፒየንስ ሊጉ 5 ክለቦችን እያሳተፏ ባለበት በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ማሳተፍ አግባብ አይደለም ነው ያሉት ።
ሻምፒዮን የሚሆን ቡድን ሊፈቀድለት የሚገባው በዛው በዩሮፓ ሊግ መሳተፍ እንጂ በቻምፒየንስ ሊግ መሆን የለበትም ብለዋል።
ዩሮፓ ሊጉ በአቋራጭ ቻምፒየንስ ሊግ መግቢያ መሆኑ የውድድሩ ድምቀት ቢሆንም ፍትሀዊ አይደለም ባይ ናቸው ።
በመሆኑም አወዳዳሪው አካል ደንብ እና መመሪያዎቹን ዳግም ሊያጤን ይገባል ብለዋል ።
