በአፍሪካ ትልቁና ዘመናዊው የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት ከ457 በላይ በተለያየ የአቪዬሽን መስክ ያሰለጠናቸውን የአቪዬሽን ባለሙያዎች አስመርቋል።
ባለሞያዎቹ የሰለጠኑባቸው መስኮችም በአውሮፕላን በረራ ፣ በቴክኒክ እና በበረራ አስተናጋጅነት መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አቬሽን ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የመጡ ዜገጎችን ጭምር በአቪየሽን መስክ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ከእዚህ ውስጥም የዩጋንዳ፣የማዳጋስካር፣የናይጄሪያ ፣ የኮትዲቫር ፣የሩዋንዳ፣የሴኔጋል ጨምሮ ከበርካታ የአፍሪ ሀገራት በተለያየ የስልጠና መርሀ ግብር ወደ ስልጠና ማዕከሉ እንደሚመጡ ተጠቁሟል።
እንዲሁም ከየመን፣ ከቻይናና ከሌሎችም ሀገሮች የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲውን መርጠው እንደሚመጡ በመድረኩ ተመላክቷል።
በመርሀ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ን ጨምሮ ዲፕሎማቶች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰብ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
