የኢትዮጵያ አየር መንገድ 21ኛውን ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን መረከቡን ገለፀ

Date:

አየር መንገዱ ዛሬ የተቀበለው ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን እጅግ ዘመናዊ እና እስከ 340 ሰዎችን መመጫን አቅም ያለው ነው።

አዲሱ አውሮፕላን አየር መንገዱ ለደንበኞች  እየሰጠ ያለውን አስተማማኝና ምቹ  አገልግሎት ይበልጥ የሚያጠናክር እና በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ያለውን የመሪነት ሚና የሚያስቀጥል ነው ተብሏል።

አፍሪካን ከዓለም በማገናኘት አንጋፋነቱን ማስቀጠል የቻለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደፊትም ሌሎች ኤርባስ A350-900 እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ለመቀበል በሂደት ላይ ይገኛል።

የስታር አሊያንስ አባል የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመንገደኞች፣  በጭነት፣  በመስተንዶ፣ ለደንበኞች አስተማማኝ አገልግሎት በመስጠት በርካታ ሽልማቶችን ማሸነፉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነቱን እና መሪነቱን ለማስቀጠል በ10 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በቢሾፍቱ የግዙፍ ዓለመ አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...