IFJ ዘጠኝ የዶይቼ ቬለ አማርኛ ጋዜጠኞች መታገድን አወገዘ

Date:

የዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (IFJ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዶይቼ ቬለ አማርኛ ዘጠኝ ጋዜጠኞች በጊዜያዊነት ማገዱን በጽኑ አወገዘ። ውሳኔውም በአስቸኳይ እንዲቀለበስ ጥሪ አቅርቧል።

ፌዴሬሽኑ ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጋዜጠኞቹን “ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በመጣስና የሀገሪቱን ደንቦችን በመተላለፍ” ከሷል።

ፌዴሬሽኑ ይህንን እርምጃ የዶይቼ ቬለን ዘገባ “ዝም ለማሰኘትና በተለይም በአማራ ክልል ውስጥ ስላለው ግጭት ኢትዮጵያውያን ገለልተኛ መረጃ እንዳያገኙ ለመገደብ የታበ የማስፈራሪያ ድርጊት ነው” ሲል ገልጾታል።

የዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ አንቶኒ ቤላንገር፣ “የዶይቼ ቬለ ጋዜጠኞች በባለስልጣኑ መታገድ ኢትዮጵያውያንን በአማራ ክልል ስላለው ግጭት እውነተኛ ዘገባ እንዳያገኙ ለማድረግ ሆን ተብሎ የተፈጸመ የማስፈራራት ድርጊት ነው” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...