የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ለእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን አስጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ለሀገር ሉዓላዊነትና ለነፃነት ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች ታሪክ ለፕሬዚዳንቱ ተብራርቶላቸዋል።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባተላለፉት መልዕክት፤ ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለነበራቸው ቆይታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማና ስኬታማ እንዲሆን በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነም ታምኖበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...