የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በጋዜጣ እስኪታተም ረቂቅ ሰነዶችን ከመጠቀም እንዲቆጠብ የፍትሕ ሚኒስቴር አሳሰበ

Date:

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በይፋ እስኪወጣ ድረስ፣ ሕዝቡና ባለድርሻ አካላት በትዕግስት እንዲጠባበቁና ይፋዊ ያልሆኑ ረቂቅ ሰነዶችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት አገልግሎት ላይ የቆየውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ የሚተካውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማጽደቁ ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት የጸደቀው ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ሙሉ በሙሉ ወደ ተፈጻሚነት እንዲገባ ለማስቻል፣ የመጨረሻው የቃላት ማስተካከያ እና ሌሎች የሕግ አርትኦት ሥራዎች (Editorial Works) በምክር ቤቱና በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል በከፍተኛ ጥንቃቄና ፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ሕጉ ለሕዝብ በይፋ ባልተሰራጨበት ሁኔታ፣ በተለያዩ ጊዜያት ሲዘጋጁ የነበሩ የሕጉን ረቂቅ ሰነዶች ለተለያዩ ሙያዊ፣ ተቋማዊ አገልግሎቶች እና ሥልጠናዎች በጥቅም ላይ የማዋል ዝንባሌዎች በተለያዩ አካላት ዘንድ መታዘባቸውን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

የመጨረሻው የአርትኦት ሥራ ሳይጠናቀቅ ማንኛውንም ይፋዊ ያልሆነ ሰነድ ለሥራ ማስፈጸሚያነትም ሆነ ለሌሎች ተግባራት ማዋል፦

በአፈጻጸም ላይ የቃላትና የአንቀጾች አለመጣጣምን ያስከትላል።

በርካታ ችግሮችን በመፍጠር በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ መደናገርን ሊፈጥር ይችላል።

በመሆኑም ይፋዊው ሰነድ እስኪወጣ ድረስ ከእንዲህ መሰል አጠቃቀሞች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የፍትሕ ሚኒስቴር በጥብቅ አሳስቧል።

የፍትሕ ሚኒስቴር የመጨረሻው የአርትኦት ሥራ ሲጠናቀቅ ሕጉ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ለሕዝብ ተደራሽ የሚሆን መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም በሚኒስቴሩ ድረ-ገጽና በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ላይ ወዲያውኑ በሶፍት ኮፒ (Soft Copy) በይፋ እንደሚጋራ አስታውቋል።

በመጨረሻም፣ ለፍትሕ ሥርዓቱ ወጥነት ሲባል ሕጉ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እስኪወጣ ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የሕግ ባለሙያዎች በትዕግሥት እንዲጠባበቁና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...