በ2019 የተከፈተው የቤጂንግ ዳክሲንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ (PKX)፣ በዓለም ትልቁ ባለ አንድ ሕንጻ ተርሚናል ቢሆንም፣ ባዶ ሆኖ መገኘቱ ተዘግቧል።
አውሮፕላን ማረፊያው በ2040 ከ100 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ለማስተናገድ ቢታቀድም፣ አሁን ላይ አብዛኛው የግብይት ማዕከሉ ክፍት እንዳልሆነ እና ተሳፋሪዎችም እንደሌሉ የጉዞ ቪሎገር የሆነው ስቴፋን ዱሪ ባሳየው ቪዲዮ ታይቷል።
ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት፣ መንገደኞች ከከተማው ጋር ቅርብ የሆኑ ሌሎች አውሮፕላን ማረፊያዎችን መጠቀማቸው ነው።
በ 11.4 ቢሊዮን ዶላር የተገነባዉ ይህ አውሮፕላን ማረፊያው እጅግ ዘመናዊና የደህንነት ጥበቃው ከፍተኛ ቢሆንም አሁን ላይ ተርሚናሉ በበቂ ሁኔታ ጥቅም ላይ አለመዋሉን መረጃው ያመለክታል።
KGEthiopia
