የጉምሩክ ጥፋቶችና ቅጣቶች

Date:

የጉምሩክ የትራንዚት ሥነ-ሥርዓትን አለማክበር

ማንኛውም ሰው በጉምሩክ አዋጅ ደንብና መመሪያዎች ላይ የተደነገገውን የጉምሩክ ትራንዚት ሥነ-ስርዓት ያላከበረ እንደሆነ ከ5 ሺህ ብር በማያንስና ከ20 ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጫ ይቀጣል፡፡

ከቀረጥ ነፃ በገባ ዕቃ ያለአግባብ መገልገል

ማንኛውም ሰው ከቀረጥ ነጻ ወይም በቅናሽ ቀረጥ የገባን ዕቃ የጉምሩክ አዋጅ ድንጋጌዎች በሚቃረን ሁኔታ፣ የቀረጥ ነፃ መብቱ ከተሰጠበት ዓላማ ውጪ በሌላ አገልግሎት ላይ ያዋለ ወይም ለሌላ ሰው ያስተላለፈ እንደሆነ ይቀጣል።

በተመሳሳይ፤ ዕቃው ለግል አገልግሎት እንዲውል የገባ ሲሆን፣ በማናቸውም መልኩ ከቤተሰብ ውጪ በሌሎች ሰዎች አገልግሎት ወይም ይዞታ ሥር እንዲውል ያደረገ እንደሆነ ቅጣት አለው።

ዕቃው ከቀረጥ ነፃ ሆኖ ወይም በቅናሽ ቀረጥ የገባ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የገዛ፣ የተቀበለ፣ የተገለገለ፣ ያስተላለፈ ወይም ለሌሎች ሰዎች አገልግሎት እንዲውል ያደረገ እንደሆነ ዕቃው በተያዘበት ጊዜ ወደ ሀገር እንደገባ ተቆጥሮ ለዕቃው ሊከፈል የሚገባው ቀረጥና ታክስ መከፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ የቀረጥና ታክሱን 50% የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...