የጉዞ ማስታወቂያ በረራዎች ወደ መካከለኛው ምስራቅ

Date:

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተቀያየረ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ስፍራው የሚያደርጋቸውን በረራዎች በጊዜያዊነት ሰርዟል።

ይህም የደንበኞቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ደህንነት ቅድሚያ ለመስጠት የተወሰደ እርምጃ ነው።

የተሰረዙ ከተሞች (ከአዲስ አበባ የሚነሱና የሚመለሱ)፦

  • ቤይሩት (ሊባኖስ)
  • ቴል አቪቭ (እስራኤል)
  • አማን (ዮርዳኖስ)
  • ደማም (ሳውዲ አረቢያ)

ማንኛውንም አይነት መጉላላት ለመቀነስ፣ ወደ አየር ማረፊያ ከመሄድዎ በፊት የሚከተሉትን እንዲያደርጉ በአክብሮት እንመክራለን፡

  • የአየር መንገዱን ድህረ ገጽ ወይም የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም የበረራዎን ሁኔታ ያረጋግጡ።
  • ቲኬትዎን በጉዞ ወኪል የቆረጡ ከሆነ ወኪልዎን ያነጋግሩ።
  • ቀጥታ በአየር መንገዱ የቆረጡ ከሆነ reservation@ ethiopianairlines. com ላይ ኢሜይል ያድርጉ ወይም በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ያነጋግሩ።

ማሳሰቢያ፦ ተጓዦች በነፃ የመቀየር (Rebooking) ወይም ሙሉ ገንዘብ የመመለስ (Refund) መብት አላቸው።

ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተልን ሲሆን፣ በረራዎች እንደገና ሲጀመሩ የምናሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር አሊያንስ አባል!

https://www.facebook.com/share/17GN9GGNKt/?mibextid=wwXIfr

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...