የሀገራትን የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ደረጃ የሚገመግመው የ’2025 ግሎባል ሀንገር ኢንዴክስ’ ጥናት በአፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት በይፋ ተመርቋል።
በጥናቱ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ እንደተገለጸው፣ ዓለም ባለፉት ዓመታት በርሀብ ቅነሳና በምግብ ዋስትና ረገድ ተስፋ ሰጪ ስኬቶችን አስመዝግቦ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ከፍተኛ መሰናክሎች ተደቅነውበታል።
በተለይም በየአካባቢው የሚቀሰቀሱ ግጭቶች፣ እየተባባሰ የመጣው የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ተያያዥ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ቀውሶች የዘርፉን ጥረቶች እንዲጓተቱ ማድረጋቸው ተመላክቷል።
በመሆኑም ይህንን ፈታኝ ወቅት ለማለፍና የተጋረጡ ስጋቶችን ለመቀልበስ፣ በዘርፉ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች በአዲስ ቁርጠኝነትና ስልታዊ በሆነ አመራር ሊደገፉ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።
ወቅታዊው ሪፖርት ሀገራት የረሀብን አዙሪት ለመስበር ፖሊሲዎቻቸውን እንዲከልሱና ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያሳስብ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፏል።
