የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ እና እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ታሪካዊ ተጨዋች ዴቪድ ቤካም የክብር ማዕረግ ስም ሊሰጠው መሆኑ ተገልጿል።
ዴቪድ ቤካም በሚቀጥለው ሳምንት በእንግሊዝ ንጉሥ ቻርልስ ” የልደት ቀን የክብር ዝርዝር ” ላይ ” Sir ” የሚል ማዕረግ እንደሚሰጠው ተገልጿል።
በተጨማሪ ባለቤቱ ቪክቶሪያ ቤካም ” እመቤት ቤካም ” የሚል ማዕረግ እንደሚሰጣት ተነግሯል።
ቤካም ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን 115 ጨዋታዎች በማድረጉ እና በበርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፉ ለአመታት የክብር ስሙ እንዲሰጠው ሲጠየቅ ነበር።
የቀድሞ የሶስቱ አናብስት አምበል ዴቪድ ቤካም የንጉሡ ፋውንዴሽን አምባሳደር በመሆንም እያገለገለ ይገኛል።
@tikvahethsport
