ኤርትራውያን በጣም ብልሆች ናቸው የፌደራል መንግስትን በቀጥታ የመዋጋት የሰው ኃይል ብልጫ እንደሌላቸው ያውቃሉ።
ስለዚህ፣ ሀገሪቱን ለማናጋት በድንበራቸው ማዶ ያሉ ‘ጠቃሚ ሞኞችን’ (useful idiots) መጠቀም ይፈልጋሉ። አሁን ያለው የህወሓት አመራር ለማድረግ እየሞከረ ያለው፣ ከፌደራል መንግስት ይመጣል ብለው ከሚያስቡት እውነተኛ ወይም ምናባዊ ስጋት እራሳቸውን ለማዳን፣ ከኤርትራውያን ጋር ህብረት መፍጠር ይቻል እንደሆነ ማየት ነው።”
“የፕሪቶሪያን ስምምነት የፈረምነው… የፖለቲካ አመራሩ (እኔንም ጨምሮ) ትልቅ ስህተት ውስጥ ስለገባና ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ስለሆኑ ነው። ስለ ጦርነቱ አካሄድ ብዙ የተሳሳቱ ስሌቶችን ሰርተናል።”
- ጌታቸው ረዳ፣ የቀድሞው የCNN እና ሮይተርስ ጋዜጠኛ ጂም ስቴንማን በሚያዘጋጀው “Global Power Shift” ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ
Via zehabesha
