ግብፅ ለኤርትራ የመሠረተ ልማት ግንባታ ልታሰማራ ነው

Date:

የግብፅ በኤርትራ ውስጥ ለሚከናወኑ የኢንዱስትሪ እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ የቴክኒክ ባለሙያዎችን ለማሰማራት እና ዝርዝር የአዋጭነት ጥናቶችን ለማካሄድ መዘጋጀቷን አስታወቀች።

ይህ የተነገረው የግብፅ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ካሊድ ሀሺም ከኤርትራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በካይሮ ባደረጉት ስብሰባ ወቅት ነዉ።

​ሚኒስትር ካሊድ ሀሺም እንደገለጹት፣ ግብፅ ያላትን የኢንዱስትሪ ልምድ ለኤርትራ በማካፈል በአገሪቱ ስልታዊ የሆኑ ፋብሪካዎች እና የመሠረተ ልማት አውታሮች እንዲገነቡ ድጋፍ ታደርጋለች።

በተጨማሪም ግብፅ በኤርትራ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከላትን በመገንባት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እንቅፋቶች በመቅረፍ ረገድ የበኩሏን ድርሻ ለመወጣት ተስማምታለች።

ይህም በቀይ ባሕር ቀጣና ያለውን ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...