ግብፅ በ1979 ከእስራኤል ጋር ባደረገችው የሰላም ስምምነት መሠረት ከተፈቀደው ቁጥር በእጥፍ የሚጠጋ 40,000 ወታደሮችን ወደ ሰሜን ሲና አሰማርታለች።
ግብፅ ወታደሮቿን ያሰማራችው እስራኤል በጋዛ የምታደርገው ወታደራዊ ዘመቻ ፍልስጤማውያንን ወደ ግብፅ ግዛት ማፈናቀልን ሊፈጥር ይችላል በሚል ስጋት ነው።
ወደ ሲና ያቀናው የግብፅ ጦር የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን፣ የአየር መከላከያ ዘዴዎችን እና ልዩ ሃይሎችን ያካተተ ሲሆን በ ራፋህ እና ሼክ ዙዋይድ ባሉ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ ሰፍረዋል።
እስራኤል ግብፅ ወታደሮቿን በማስጠጋቷ ደስተኛ እንዳልሆነች የገለፀች ቢሆንም ግብጽ እራሴን ለመከላከል ያደረኩት እርምጃ ነው ብላለች።
