የኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን የሰላም ምክር ቤት በማቋቋም ከሰላም ሚኒስቴር ጋር እየሰራ መሆኑን ለአሐዱ ገልጿል።
የፌደሬሽኑ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አስካለ ለማ፤ “ችግሮች ሲኖሩ ግጭቶች ሲፈጠሩ በውይይት ለመፍታት ከማመቻቸት ጀምሮ ስራዎችን እየሠራን ነው” ብለዋል።
“እንዲሁም ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት የመከላከል ሥራ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ይሠራሉ” ያሉ ሲሆን፤ በሰላም መደፍረስ ውስጥ ከማንም በፊት ተጎጂ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይም ከሰላም ጠቃሚ የሚሆኑትም ሴቶች መሆናቸውን በማንሳት፤ ሴቶችን ለሰላም ዘብ የማድረጉ ሥራ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ፌደሬሽኑ የተለያዩ ውይይቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ማድረጉን አንስተዋል።
በተያያዘም “ለሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ሥራዎችን በማመቻቸት፣ የብድር አገልግሎት፣ የሥራ ቦታ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ ነው” ብለዋል።
እንዲሁም የማህበራዊ፣ በጤና እና በትምህርት ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
(አሐዱ ሬድዮ)
