ፑቲን “የአባትዎትን ሥራ እንደሚያስቀጥሉ እተማመናሁ” አሉ

Date:

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት ሌሊት ለተመረጡት አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ። ፑቲን፤ ሩሲያ ለኢራን ያላትን “የማይናወጥ አጋርነትም” በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ፑቲን የክሬምሊን ድረ ገጽ ላይ በወጣ መልዕክታቸው፤ “እባክዎት፤ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ ሆነው በመሾምዎ ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክቴን ይቀበሉኝ” ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ፤ ሩሲያ “ለቴህራን ያላትን ድጋፍ እንዲሁም ከኢራናውያን ወዳጆቻችን ጋር ያለንን አጋርነት አረጋግጣለሁ” ብለዋል። “ታማኝ አጋር ሆኖ ለመቀጠልም” ቃል ገብተዋል።

“ኢራን በትጥቅ የታገዘ አመጻ እየተጋፈጠች ባለችበት በዚህ ጊዜ፤ [በተረከቡት] ከፍተኛ ሥልጣን የሚወስዱት እርምጃ ያለ ምንም ጥርጥር ትልቅ ድፍረት እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል” ሲሉ ለአዲሱ ጠቅላይ መሪ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፑቲን መልዕክታቸው፤ “የአባትዎን ስራ እና ከፍተኛ መከራ የተደቀነበትን የኢራን ሕዝብ አንድነት በክብር እንደሚያስቀጥሉ እተማመናለሁ” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...