👉 በአዲስ አበባና ጎንደር ከተሞች አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በቅድመ ጥገና ሥራ ምክንያት ዛሬ ኃይል ተቋርጧል
ሲስተም ላይ ባጋጠም ብልሽት ምክንያት 905 እና 904 ነፃ የጥሪ ማዕከሎች እንዲሁም የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን ጨምሮ ከኢንተርኔት አገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የድህረ ክፍያ አገልግሎቶች አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
ችግሩ ተፈትቶ የተቋረጠው አገልግሎት እስከሚመለስ ድረስ ደንበኞች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዲስትሪክቶች ወይም አገልግሎት መስጫ ማዕከሎች በአካል ወይም በቀጥታ ስልክ በመደወል ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሚያከናውነው የቅድመ ጥገና ሥራ ምክንያት፤ በአዲስ አበባና ጎንደር ከተሞች አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በዕቅድ የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 9:30 እንዲሁም፤ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18፣ ሻዋ ዳቦ፣ ኮሌጅ፣ ባህር ሰላም እና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡