እኤአ ከ2010 ጀምሮ በአመቱ ውስጥ አስደናቂ እንቅስቃሴን ላደረጉ ተጫዋቾች ፣ እንዲሁም አሰልጣኞች እና በተለያዩ ወርፎች ሽልማት የሚሰጥ እና በቶማሶ ቤንዶኒ መስራችነት የተቋቋመ የሽልማት ዘርፍ ነው።
ይህ የሽልማት ዘርፍ ለየት የሚያደርገው የአንድ ቡድን ጀርባ ወሳኙን ስራ የሚሰሩት የቡድም ቴክኒካል ዳይሬክተሮች ከዛ ውጪ የአመቱ ምርጥ ወኪል በሚል ለተጫዋቾች ወኪል የሚሰጥ ሽልማት እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ ወይም የባህረ ሰላጤውን የሳውዲ ሊግ ላይ ጥሩ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ተጫዋቾችን የሚሸልም የሽልማት መድረክ ነው።
የዚህ አመት እጩዎች ይፋ የተደረጉ ሲሆን አሸናፊዎቹ በሳውዲ አረቢያ the atlantis royal hotel ዱባይ ላይ በሚዘጋጀው የሽልማት መድረክ ላይ ሽልማታቸውን በአካል በመገኘት ተቀብለዋል።
በዚህም መሰረት የአመቹ ምርጥ ወንድ ተጫዋች (Best Men’s Player): በዚህ ምድብ 22 እጩዎች የነበሩ ሲሆን ፣ የፓሪስ ሴንት ጄርሜው ኡስማን ዴምቤሌ አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል።
የአመቱ ምርጥ ተስፈኛ ወጣት ተጫዋች በሚለው ዘርፍ የፓሪስ ሴንት ጄርሜው ዴሳየር ዱዌ አሸናፊ ሆኗል።
የአመቱ ምርጥ የፊት መስመር ተጫዋች በሚለው ዘርፍ የባርሴሎናው ላሚን ያማል አሸናፊ በመባል ተመርጧል።
ምርጥ የወንዶች ክለብ (Best Men’s Club): ለምርጥ ክለብነት የተመረጡት ስምንት ቡድኖች መካከል በውድድር ዘመዩ የ5ዮሽ ዋንጫን ያሳኩት የፈረንሳዩ ሀያል ቡድን ፓሪስ ሴንት ዠርሜ ተመርጠዋል።
የአመቱ ምርጥ ፕሬዚዳንት የፓሪስ ሴንት ጄርሜው ባለቤት እና ፕሬዚዳንት ኳታራዊው ቢሊየነር ናስር ኤል ሄላፊ ሲመረጥ ምርጥ ቴክኒካል ዳይሬክተር በሚለውም ዘርፍ የዚሁ ክለብ እየሰራ የሚገኘው ፖርቹጋላዊው ልዊ ካምፖስ አሸናፊ በመሆን ተመርጧል።
ምርጥ ወኪል በሚለው ዘርፍ ፖርቹጋላዊው ሆርጌ ሜንዴዝ ፣ የምሽቱ ልዩ ተሸላሚ በቅርቡ ህይወቱ ያለፈው የሊቨርፑሉ ኮኮብ ዲዬጎ ጆታ እንዲሁም ወደ ራስ መመለስ እና ጥሩ አመጣጥ ወይም best comeback በሚለው ዘርፍ ከአበረታች ንጥረ ነገሮች ጋር በተያያዘ ለአመት ታኩል ለሚሆን ጊዜ ከሜዳ ርቆ የቆየው ፖል ፓግባ ተመርጦ አሸናፊ ተብሏል።
የአመቱ ምርጥ አማካኝ የብዙዎችን ቀልብ በውድድር ዘመኑ የሳበው ፖርቹጋላዊው ቪቲንሀ አሸናፊ በመሆን ተመርጧል።
ምርጥ የሴቶች ተጫዋች (Best Women’s Player): የባርሴሎናዋ አይታና ቦንማቲ ለሶስተኛ ተከታታይ አመት ሽልማቱን መውሰድ ችላለች።
ምርጥ የሴቶች ክለብ (Best Women’s Club): አርሰናል፣ ባርሴሎና፣ ባየር ሙኒክ፣ ቸልሲ፣ ዩቬንቱስ፣ ሊዮን እና ኦርላንዶ ፕራይድ በእጩነት ቀርበው የባርሴሎና ሴቶች ቡድን አሸናፊ በመባል ተመርጧል።
ምርጥ የመካከለኛው ምስራቅ ተጫዋች (Best Middle East Player): በሚለው ዘርፍ ፖርቹጋላዊው ኮኮብ ክሪቲያኖ ሮናልዶ ተመርጧል።
ይህንን የሽልማት መድረክ በተለያዩ ዘርፎች 17 ጊዜ በማሳካት ፖርቹጋላዊው ኮኮብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከፊት የሚጠቀሰው ተጫዋች ነው።
ባጠቃላይ የእግርኳስ ቤተሰቡ ይገባቸዋል ብለው ለሚያስቡት የስፖርት ሰው ድምጽ የሰጡ ሲሆን ፤ የመጨረሻ አሸናፊዎች የተወሰኑት በደጋፊዎች ድምጽ እና በባለሙያዎች ዳኝነት ድምር ውጤት ነው ተብሏል።
