የድምጻዊት የማ የሙዚቃ ቪዲዮ ተለቀቀ

ድምጻዊት የማርያም ቸርነት(የማ) “ስንት ነው?” ለተሰኘው የሙዚቃ ሥራዋ ያስናዳችው የሙዚቃ ቪዲዮ  መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዩቲዩብ ቻናሏ በኩል ለአድማጮች ደርሷል።

ድምጻዊት ስለዚህ የሙዚቃ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገጿ”የደጋ ሰው አልበም ከተለቀቀ አንድ ዓመት የሆነው ሲሆን በዚህ መካከል በነበሩኝ 70 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ የመድረክ ስራዎች እና ዝግጅቶች  ምክንያት የቪዲዮ ስራ ሳላቀርብ ቆይቻለሁ።

በቅርቡ በአዲስ አበባ በመድረክ የምንገናኝ ሆኖ ከዚህ አልበም ውስጥ “ስንት ነው? “የተሰኘውን የሙዚቃ ቪዲዮ በየማ (YEMa) YouTube channel ስለተለቀቀ እንድትመለከቱት እና ከወደዳችሁት እንድታጋሩት እጋብዛለሁ” ብላለች።

በዚህ የሙዚቃ ላይ ጎላ ጎህ  በግጥም  የተሳትፈ ሲሆን በዜማ፣ ቅንብር፣ ቀረፃ እና ድምፅ ውህደት ኢዩኤል መንግስቱ ተሳትፏል።