የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፈዴሬሽን 41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ውድድር ነገ 29/10/2017 ዓ.ም በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል ።
ዛሬ ፌዴሬሽኑ ከክለብ አሰልጣኞች ፣አትሌቲክስ ዳኞች፣ቡድን መሪዎች ፣የህክምና ባለሙያዎች እና ከክልሉ የፀጥታ አካላት ተወካዮች ጋር በሀዋሳ ከተማ የቴክኒክ ስብሰባ አከናውኗል ።
👉በውድድሩ ላይ ክልልና ከ/አስተዳደሮች 2 ፣ክለቦች 10 እንዲሁም አንጋፋ አትሌቶችና የግል ተወዳዳሪዎች ሴት 94፣ ወንድ 288 በአጠቃላይ 364 አትሌቶች ይሳተፋሉ ።
👉ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ በቂ በጀት መድበዋል ።
👉በአጠቃላይ ለውድድሩ የሚመሩ በአለም አትሌቲክስ ደረጃ ስልጠና የወሰዱ 70 ዳኞች ተመድበዋል ።
👉የፌዴሬሽኑ ስፖንሰሮች ኢትዮ ቴሌኮም፣ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ካምፓኒ ኮካኮላ እና ኦሮሚያ ባንክ ውድድሩ በታላቅ ድምቀት እንዲካሄድ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ።
👉 ውድድሩ ሰፊ የሚድያ ሽፋን የሚያገኝ ሲሆን፣ ፌዴሬሽኑ ከ20 በላይ የመገናኛ ቡዙሃን ባለሙያዎች ለስፖርት ቤተሰብ መረጃ ለማድረስ ወደ ስፍራው ተጉዘዋል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የስልጠና ጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንስትራክተር አድማሱ ሳጂ ፣የሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ አስራት አሰፋ፣የፌዴሬሽኑ ውድድር እና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ እና የፌዴሬሽኑ የፋሲሊቲ ዳይሬክተር አቶ አሰፋ በቀለ በጋራ በመሆን ውይይቱን መርተውታል ።
የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና አቃቤ ነዋይ ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ ፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአትሌቶች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ ጨምሮ የፌዴሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት እና ሰራተኞች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል ።
የ15 ሺህ 960 ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቀቀ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የ15 ሺህ 960 ፕሮጀክቶች ግንባታ ተከናውኗል አለ የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፡፡
የቢሮው ኃላፊ እናትአለም መለስ በሰጡት መግለጫ ÷ በበጀት ዓመቱ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 15 ሺህ 960 ፕሮጀክቶች ከነገ ጀምሮ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋሉ ብለዋል፡፡
ከተሰሩት ፕሮጀክቶች መካከል በዋናነት የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ከ10 ሺህ በላይ ቤቶች መገንባታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
በበጀት ዓመቱ የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላት የተገነቡት ቤቶች በመንግስት እና በሕብረተሰቡ ትብብር መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በአጠቃላይ የማሕበረሰቡን ማህበራዊ እንቅስቃሴ የሚያግዙ የጤና፣ የትምህርት እና የመንገድ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል ነው ያሉት ሃላፊዋ።
የከተማዋን ወጣቶች ጥያቄ ለመመለስ 122 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የተገነቡ ሲሆን ÷ ለ366 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡
በአረንጓዴ ልማት ሥራ በ517 ሔክታር ላይ 245 ፕሮጀክቶች የተገነቡ ሲሆን÷ ከእነዚህ መካከልም ፓርኮች፣ ፕላዛዎች እና የመንገድ አካፋዮች ይገኙበታል ነው ያሉት፡፡
በሌላ በኩል 246 ኪሎ ሜትር የእግረኛ እና 141 ኪሎ ሜተር የብስክሌት መንገድ እንዲሁም 43 ኪሎ ሜትር የመሮጫ ትራክ እና 53 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ እና የመሸጋገሪያ ድልድዮች መገንባታቸውን አመልክተዋል፡፡
