ለባዊ ዓለም አቀፍ አካዳሚ ” ትውልድን በስነ ጽሑፍ ማስተሳሰር ” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የመጻሕፍ አውደ ርእይ እና የውይይት መድረክ ላይ 56 ዓመት ያስቆጠረው የዕውቀት በር የመጻሕፍ መደብር ተመሰገነ።
በዚህ የለባዊ አካዳሚ የተማሪዎች ካውንስልና የቤተ መጻሕፍ ሰራተኞች በጋር በመሆን በአዘጋጁት መድረክ ላይ ነው የዕውቀት በር መጻሕፍ መደብርን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው አቶ ደመላሽ ከበደ የአባቱን ርእይ በማስቀጠል ለአደረገው አበርክቶ ከለባዊ ዓለም አቀፍ አካዳሚ የምስጋና ሰርተፍኬት የተሰጠው።
በምስጋና መድረኩ ላይ እንደ ደምመላሽ ከበደ የቤተሰብን ርእይ የሚያስቀጥሉና ንባብ ባህል እንዲሆን የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ያስፈልጉናል ተብሏል።
አካዳሚው የአዘጋጀውን የአውደ ርእይና የውይይት መድረክ በንግግር የከፈቱት የለባዊ መስራች እና ዳሬክተር ፓኖስ ሐዛንድሪያስ (ፕ\ር) በንግግራቸው ለባዊ አንባቢ ተማሪዎችን ለማፍራት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ ይህ ደራሲያንን ፣ አሳታሚያንን እና ባለመደብሮችን እየጋበዘ የሚያዘጋጀው የውይይት መድርክ ነው ብለዋል።
በዕለቱ የተጋበዙት ጸሐፌ ተውኔትና ገጣሚ ኃያልነህ ሙላት፣ የፀሐይ አሳታሚ መስራችና ስራ አሰኪያጅ አቶ ኤሊያስ ወንድሙ እና ባለብዙ ተሰጠዋ ወ\ት ሊያ ባፈና ሰለስነ ጽሑፍ ያላቸውን ልምድ ያካፈሉ ሲሆን ስለየዕውቀት በርም ታሪክ ለተማሪዎቹ አጋርተዋል።
ለባዊ ዓለም አቀፍ አካዳሚ ኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ አስተሳሰብን መሰረት ያደረገ የትምህርት ስርዓት ቀርጾ ልዩ ፍላጎትን ጨምሮ ከመዋለ ህጻናት እሰከ አስራ ሁለተኛ ክፍል እያስተማር እንዲሚገኝ ይታወቃል።
