65 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Date:

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጋር በመቀናጀት በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን በተቋሙ ቢሮ አካባቢ በመሆን በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 65 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ።

ተጠርጣሪዎች በተለያየ የህገ-ወጥ የድለላ ስራዎች ላይ የተሰማሩ፣ የስራ ከባቢውን በማወክ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር እየፈጠሩ ያሉ፣ በተለያየ የማጭበርበር እና የማታለል ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና በህገ-ወጥ መንገድ የኦን ላይን የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ መሆናቸው ተገልፆል።

በአጠቃላይ 7 በህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማሩ ቤቶች መታሸጋቸውን እና 65 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑ ተነግሯል። ከእነዚህም መካከል 25 ቱ ሴቶች እንደሆኑ ታውቋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...