75% የአዲስ አበባ ነጋዴዎች የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት አላገኘም ተባለ

Date:

75 በመቶ የሚሆኑ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ ደረጃውን ያልጠበቀ እና በሙያ ብቃት በሌላቸው ሰዎች የሚዘጋጅ በመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ከአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና ከነጋዴ ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት፣ በጥቅምት ወር በተካሄደው ቅድመ ኦዲት 25 በመቶ ያህሉ ነጋዴዎች ብቻ የሂሳብ መዝገባቸው ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጧል።

የተቋሙ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ እንደገለጹት፣ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ በባንክ ሂሳባቸው ከሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ጋር የማይጣጣም ነው። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በባንክ አካውንታቸው ላይ ቢታይም፣ በሂሳብ መዝገባቸው ላይ ምንም ትርፍ እንዳላገኙ ያሳያሉ።

አንዳንዶቹ ደግሞ ገንዘቡን በህጋዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ወጪ አድርገው ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም የተባለ ሲሆን የሚመጣው የሂሳብ መዝገብ ፕሮፌሽናል ባልሆኑ ሰዎች እየተዘጋጀ ነጋዴው ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑም ተገልጿል።

Via Capital

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...