በምረቃ ቀኑ ‘ ዘረኛው ልባችን ‘ የተሰኘ መፅሐፍ አስመረቀ

Date:



በማተሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪግ ትምህርት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመረቀው፤ በተመሳሳይ በምረቃ ቀኑ ” ዘረኛው ልባችን ” የተሰኘ መፅሐፍ ያስመረቀውና በእለቱ መፅሐፉን ተዘዋውሮ ሲሸጥ የተስተዋለው ወጣት ሁዋድ ረሻድ የብዙኃኑን ቀልብ ስቧል።

ትምህርትና ድርሰቱን በአንዴ እንዴት እንዳስኬደው፣ ለድርሰቱ ምን እንዳነሳሳው በመጠየቅ ቲክቫህ ወጣቱን አነጋግሮታል።

ሁዋድ ረሻድ ፦

” አማርኛ ቋንቋ ሙሉ ለሙሉ ለመናገር የሚቸገር አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የጤና እክል ገጥሞት ክሊኒክ ሄዶ ነበር። በወቅቱ ያገኛቸው የክሊኒኩ ሰዎች ደግሞ ከአማርኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ ስለማይናገሩ ተማሪው የህመም ስሜቱን ለማስረዳት በተቸገረበት ቅጽበት መመልከቴ የድርሰቱ መነሻ ሆኖኛል።

ከዘር ፓለቲካ በመነሳት ተማሪዎች ከየተወለዱበት ክልል ስሌላኛው ክልል ስለሚሰሙት ነገር በአእምሯቸው የሚቀርጹት አመለካከት ጤነኛ ባለመሆኑ ይሄው ተማሪም ይህ አይነት እሳቤ ስላለው የክሊኒኩን ሰዎች ለደኀንነቱ በመስጋቱ የሚችለውን ቋንቋ እንኳ ደፍሮ ለመገር አልፈቀደም።

በወቅቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተግባብተን ታማሚውን ረዳውት። 

ተማሪው ባጋጣሚ የዶርም ጓደኛዬ ሆነ፤ ከተግባባን በኋላ በጣም ልብ የሚነካ ነገር አጫወተኝ። ግቢ እንደገባ ዶርም ውስጥ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ የማይተኛ እንደነበርም ነገረኝ። የማይተኛው ሰዎች ‘ሊገድሉኝ ቢሞክሩ እንኳ ገድዬ እሞታለሁ ‘ በሚል እሳቤ ነው።

‘ከብሔሬ ውጪ ያሉ ሰዎችን በብሔራቸው ለይቼ ብቻ አሳድጀ ገርፌ አውቃለሁ’ ብሎ እየጸጸተ አጫውቶኛል።

ይህ ሰው ይህን ያደረገው የተነገረውን መጥፎ ታሪክ ሙሉ ለሙሉ ስላመነበት ነው። ስለዚህ ታሪክ አእምሮን ሼፕ ያደርጋል፤ ሌሊቱን ሙሉ እስካለመተኛት ያደረሰው የተየገረውን ነገር በማመኑ ነው።

ከዚህ በመነሳት የሰው ልጅ መጥፎ ታሪክ በተነገረውና ወደ ውስጡ ባሰረጸው ቁጥር መጥፎ አስተሳሰብ እንደሚላበሰው ሁሉ ጥሩ ነገር ቢነገረው ጥላቻን ተጸይፎ እንዲኖር ማድረግ ይቻላል። በዚሁ አውድ ነድ ‘ ዘረኛው ልባችን ‘ በሚል ርዕስ መፅሐፍ ለማሳተም የበቃሁት። ” ብሏል።

በመፅሐፉ ምን ሊያስተምረን እንደፈለገ የተጠየቀው ወጣቱ እንዲህ ሲል አብራርቷል።

” የሰው ልጅ ጊዜና ቦታ ሳይገድበው ማዳንም ሆነ መግደል፤ መውደድም ሆነ መጥላት ይችላል። መጥላት የቻለ ልብ ፍቅርን/መዋደድን መለማመድ አያቅተውም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ መውደድ በልቡ ዙፋን ማንገስ የሚፈልግ ሁሉ ዘረኛው ልባችን መፅሐፍን ያንብብ።

በብሔርተኝነት በመከፋፈል፣ አንዱን እንግዳ ተቀባይ፣ አንዱን ዘራፍ ባይ ሲደርግ ይስተዋላል። ለምሳሌ የድሬና የጎንደር ሰው ተጫዋች አድርገን እንወስዳልን በተለምዶ፤ ግን አንተ ነህ አካባቢውን የምትመስለው፤ ባሕር ዳር አንድ ቀን አድሬ ጅማ የምመለስ ከሆነ አንተን ካገኘሁ ባሕር ዳርን የምመስላት በአንተ ነው። ሰዎች ክልልን፣ ብሔርን እየገለጹ ያሉት ባገኙት ሰው ልክ ነው።

ለልብ የሚከብደው መጥላት ነው። ሰው መጥላት ከቻለማ መውደድ አያቅተውም። “

ደራሲው በመፅሐፉ፣ ዘረኝነት በሰዎች አመለካከት የሚመጣ በመሆኑ አመለካከታችን ከተቀየረ በብሔር ያለመሳቀቅ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይቻላል የሚል ሙሉ ተስፋ አለው።

ደራሲውን ለማግኘት ይደውሉ
0924807351@tikvahethmagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...