የኢራንና ሳውዲ ግንኙነት

Date:

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ሳውዲ አረቢያ ገብተዋል፡፡

ከሳውዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን (ኤም ቢ ኤስ) ጋር  በጅዳ ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ማድረጋቸውም ተሰምቷል።

ሰይድ አባስ አራግቺ ከ12 ቀናቱ ጦርነት በኋላ ወደ ሳውዲ አረቢያ ብቅ ሲሉ የመጀመሪያቸው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ቴህራን እና ሪያድ ዲፕሎማሲያው መንገዶችን እያጠናከሩ መሄዳቸውን የሚጠቁም ጉዞ ተደርጎ ሲወሰድ፣ አገራቱ ቻይና ካሸማገለቻቸው ወዲህ በመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ውስጥ ሚናቸውን የጋር እያደረጉት እንደሆነ ያሳያልም ተብሏል።

ስለአሁናዊ የቀጠናው ሁኔታዎች እና ስለተፈጠሩ አዳዲስ ነገሮች የተወያዩ ሲሆን፣ ልዑሉ እና አራግቺ የተሰሩ ስራዎችንም ገምግመዋል።

ውጥረቶችን ለማብረድ የተደረሰው ስምምነት ለሰላም እና መረጋጋት ትልቅ ሚና እንዳለው መሐመድ ቢን ሳልማን ተናግረዋል።

ሳውዱ አረቢያም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላማዊ የዲፕሎማሲ መንገዶችን እንደምትከተል ከመወሳቱ ባሻገር፣ የቀጠናው መረጋጋት ለሁለንተናዊ እንቅስቃሴና ዕድገት ቁልፍ ሚና እንደሚኖረውም ታሳቢ ተደርጓል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...