የሃይማኖት አባቶች ለሽምግልና ወደ መቀለ አቀኑ

Date:

ከሰባት የሀይማኖት ተቋማት የተወከሉና ከእያንዳንዱ የሀይማኖት ተቋም ሶስት ሶስት ተወካዮች በጠቅላላው 21 የሀይማኖት አባቶች በዛሬው ዕለት ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ማምራታቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል።


በቆይታቸውም ከፕሬዝዳንት ታደሰ ወረዳ እንዲሁም ከሰራዊቱ አዛዦች ጋር በሰላም ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ/ዶ/ር/ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ መናገር ትርጉም ስለሌለው ጦርነቱ ሳይጀመር የሀይማኖት አባቶች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ሽማግሌዎች ወደ ትግራይ ክልል በመሄድ ስራቸውን እንዲሰሩና እንዲያሸማግሉ ለፓርላማው መናገራቸውን አይዘነጋም።

ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ተመሳሳይ የሽምግልና ሂደት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም አለመሳካቱና ወደ ጦርነት መገባቱ የሚታወስ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...