ብራይን ምቤሞ ማነው ?

Date:

ማንችስተር ዩናይትድን በይፋ የተቀላቀለው ብራይን ምቤሞ የመልሶ ማጥቃት አጨዋወትን የሚወድ ተጫዋች ነው።

ምቤሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ለብሬንትፎርድ በሁሉም የሊግ ጨዋታዎች ( 38 ጨዋታዎች ) ተሰልፎ ተጫውቶ ሀያ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ምቤሞ በፊት መስመር በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሲጫወት ምርጥ ብቃቱን ማሳየት የቻለው ከቀኝ መስመር እየተነሳ ሲጫወት ነው።

ምቤሞ የፍፁንም ቅጣት ምት እድሎችን በመጠቀም ረገድ ጥሩ ሲሆን ካገኛቸው አስራ ሁለት እድሎች አስራ አንዱን ከመረብ አሳርፏል።

ምቤሞ በተለይም ከጉዳት ነፃ ከሚባሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆኑ ዩናይትድን ተጠቃሚ ያደርገዋል።

ተጫዋቹ ለመጨረሻ ጊዜ በጉዳት ከሜዳ የራቀው በ 2023/24 የውድድር ዘመን በቁርጭምጭሚት ጉዳት ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ለሶስት ወራት ርቆ ነበር።

ምቤሞ ባለፉት አራት የውድድር ዓመታት መጫወት ያልቻለው በአስራ ስድስት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነው።

ምቤም በ 2022 የአለም ዋንጫ ለካሜሩን ከመጫወቱ በፊት በእድሜ ቡድኖች ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫውቶ አሳልፏል።

@tikvahethsport

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...