አሜሪካን ያሰጋዉ የሩሲያና ቻይና ጥምረት

Date:



‎ሁለቱ የግዙፍ ጦር ባለቤቶች ቤጂንግ እና ሞስኮ በሩሲያ የወደብ ከተማ ቭላዲቮስቶክ አቅራቢያ አቅማቸዉንና ጉልበታቸውን የደረሱበትን የቴክኖሎጂ ምጥቀት ለአለም የሚያሳዩበት በአየር እና በባህር ላይ አመታዊ ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑ ተነገረ ።

‎የቻይና ጦር  ከሩሲያ ሀይሎች ጋር በሚቀጥለው ወር አመታዊ የጋራ የባህር ላይ ጥምር ጥበቃ እና የአየርና የባህር ላይ ልምምድ እንደሚያደርጉ ረቡዕ አስታዉቋል ።

‎የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣንግ ዢያኦጋንግ እንደተናገሩት ይህ በአየር እና በባህር ላይ የሚደረገዉ የሁለቱ ሀገራት የ2025 የጋራ ልምምድ አላማ በእስያ-ፓሲፊክ ክልል ውስጥ ከአካባቢዉ ሀገራት ጋር ወታደራዊ ልምምዶችን እንደ ሰበብ በመጠቀም በቀጠናው እግር እየተከለችና የአከባቢውን ሰላም እና መረጋጋት ለማደፍረስ እየሞከረች ለምትገኘዉ ዩናይትድ ስቴትስ የበላይነት እንደማይኖራት መልዕክት ለማስተላለፍ ያለመ ነው” ሲል ተናግሯል።

‎አክሎም የአየር ኃይሉ ልምምዱ ኃይሉን ዝግጁነት እንዲጠብቅ እና በውጥረት ውስጥ ያሉ ተልእኮዎችን እንዲፈጽም በማሰልጠን በፓስፊክ ውቅያኖስ ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋር አገሮችን የመከላከል አቅማቸውን ለማሳየት ያስችላል ብሏል።

‎ዣንግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ልምምዱ እና ጥበቃው የዓመታዊ የትብብር እቅድ አካል ነው እናም ወደ ሌላ ሀገር ያነጣጠረ ወይም ከአሁኑ ዓለም አቀፍ ወይም ክልላዊ ሁኔታ ጋር የተገናኘ አይደለም ሲሉ በአፅንኦት ገልፀዋል ።

‎በመጨረሻም የዩኤስ አየር ሃይል ከጃፓን እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በምእራብ ፓስፊክ ውስጥ እያካሄደ ያለውን ልምምዶች ተችተዋል።


‎የቻይና እና የሩሲያ መንግስታት በቅርብ አመታት ግንኙነታቸውን ያጠናከሩ ሲሆን ቻይና በሞስኮ ዩክሬን ላይ በወሰደችው ወረራ ምክንያት በምዕራቡ ዓለም የተጣለውን ማዕቀብ ለሩሲያ ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ትሰጣለች።

‎- ምንጭ፡ [ሞስኮ ታይምስና የቤጂንግ ኮሚኒኬሽን] ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...