ጣና ነሽ 2 ጀልባ አንድነታችን የታደሰባት፤ ኢትዮጵያዊ ቀለማችን ደምቆ የታየባት የኢትዮጵያውያን አንድነት ማሳያ ሆናለች ሲሉ የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለፁ።
ከጅቡቲ ዶላሬ ወደብ መጋቢት 30 የተነሳችው ጀልባዋ የኢትዮጵያን ምድር ከረገጠችበት ዕለት አንስቶ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የኔ ሀብት ናት በሚል ስሜት አቀባበል ሲያደርግላት እና ኢትዮጵያዊነቱን ሲያሳይ እንደነበር ጠቅሰዋል።
ይህን ሁሉ መንገድ አቋርጣ የመጣችው ጀልባዋ የቱሪዝም ዘርፉን እንድታነቃቃ በትጋት እንደሚሰራም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ ተናግረዋል።
