ፓላስ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫን አነሳ

Date:

በኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ ክርስታል ፓላስ ሊቨርፑልን በመለያ ምት አሸንፏል፡፡ በዌይምብሌ በተደረገው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች መደበኛ 90 ደቂቃውን ሁለት አቻ አጠናቀዋል፡፡


የሊቨርፑልን ሁለት ግቦች አዲስ ፈራሚዎቹ ሁጎ ኢኪቲኬ እና ጀርሚ ፍር,ሪምፖንግ አስቆጥረዋል፡፡ ጃን ፍሊፕ ማቴታ በፍጹም ቅጣት ምት እና ኢስማኤል ሳር በጨዋታ የክርስታል ፓስን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡


አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው መለያ ምት ክርስታል ፓላስ 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡ ሙሀመድ ሳላ እና አሌክሲስ ማክ አሊስተር የሊቨርፑልን ሁለት ተከታታይ መለያ ምትቾች መጠቀም አልቻሉም፡፡


አሰልጣኘ አርን ስሎት በዌይምብሌ ባደረጓቸው ሁለት የፍጻሜ ጨዋታዎች በሁለቱም ለመሸነፍ ተገደዋል፡፡ አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር በፓለስ ቤት 2ኛ ዋንጫቸውን አንስተዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...