በጎ ፈቃደኞችን በማሰማራት በመንግስት ይሸፈን የነበረ የ18 ቢሊየን ብር ወጪ ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ይመር ከበደ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ በ2017 በጀት ዓመት በበጎ ፈቃድ ዘርፍ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ፣ በደም ልገሳ፣ በመንገድ ትራፊክ ደህንነት አገልግሎት፣ በአካባቢ ፅዳት፣ በማዕድ ማጋራት፣ በቤት ግንባታ ተግባር በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ የኅብረተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል ሲሉ ተንግረዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋፆ ለማሳደግ በሚከናወኑ የሰው ተኮርና የበጎ ፈቃድ ተግባራት በጥቅሉ አንድ ሚሊዮን 736 ሺህ 980 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ችለናል ነው ያሉት፡፡
ጋዜጣ_ፕላስ
