በጤና ተቋማት የሚገኙ ፋርማሲዎች 100 ሜትር እንዲርቁ  ተነገረ

Date:

ከጤና ተቋማት አጠገብ አገልግሎት የሚሰጡ ፋርማሲዎች፤ ከሚገኙበት አካባቢ 100 ሜትር እንዲርቁ የሁለት ዓመት ጊዜ እንደተሰጣቸው ኢትዮቲዩብ ሰምቷል።

ውሳኔው የመድኃኒት ሽያጭ አገልግሎትን ለሁሉም ማኀበረሰብ  ተደራሽ ለማድረግ ሲባል በተዘጋጀው “የፋርማሲ ስታንዳድ” መሰረት የተወሰነ ነው ተብሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚ መሆን የጀመረውን “የፋርማሲ ስታንዳድ” ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ነው። ይህን ስታንዳርድ የማስፈጸም ኃላፊነት ደግሞ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ነው። ስታንዳርዱ የተዘጋጀው ፋርማሲዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበር “ወጥ የሆነ አሰራር ባለመኖሩ” እንደሆነ ከባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የፋርማሲ ስታንዳርዱ ከመውጣቱ በፊት ፋርማሲዎች አገልግሎት የሚሰጡት  እንደሚገኙበት ክልል በተለያየ መመሪያ ሲሆን አሁን ላይ የተዘጋጀው ስታንዳርድ ግን በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉም ፋርማሲዎች ወጥ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

ኢትዮቲዩብ የተመለከተው ስታንዳርድ፤ “የፋርማሲ ባለሙያዎችን ኃላፊነት”፣ “ታካሚዎች ማግኘት ስለሚገባቸው አገልግሎቶች” እና “ፋርማሲዎች ሊኖራቸው ስለሚገባ  የቦታ ስፋት እና ርቀት” የሚያብራራ ነው።

በዚህ መሰረት በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው ሰነድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ፋርማሲዎች ለታካሚዎች የምክር አገልግሎት የሚሰጡበት ሥፍራ የማዘጋጀት ግዴታ ጥሎባቸዋል። ይህ አሰራር ታካሚዎች ሚስጥራቸውን ጠብቀው ምክር ማግኘት እንዲችሉ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...